ለመላው ህዝበ ክርስቲያን በሙሉ

በመጀመሪያ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ እና ጥምቀቱ አደረሳችሁ እያልን በፊኒክስ አሪዞና የደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም የኢ//ተ ቤተ ክርስቲያን የጥር አስተርእዮ የድንግል ማርያምን በዓለ እረፍት ምክንያት በማድረግ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ጥር 19 – 21 /2015 (January 27 – 29) ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ አዘጋጅቷል።

       በዕለቱ ከተለያዩ አድባራት ጥሪ የተደረገላቸው አበው ካህናት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ምዕመናን በሚገኙበት በድምቀት ይከበራል።       

መርሃ ግብር

        ዓርብ 1/27/23 4:00 PM ጀምሮ ሥርዓተ ዋዜማ

        ቅዳሜ 1/28/23

       ከ400AM ጀምሮ   በሥርዓተ ማኅሌት ተጀምሮ        የንግሥ በዓል ይካሄዳል።

        እሁድ 1/29/23  ከ 500 AM  ጀምሮ ጸሎተ ኪዳን፣ ጸሎተ ቅዳሴ እና ትምህርተ ወንጌል ይካሄዳል። ስለዚህ ይህን አውቀው በዕለቱ በመገኘት የድንግል ማርያም በረከት ተሳታፊ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ስም መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።