የህንፃ ኮሚቴ መምረጥን በተመለከተ

1ኛ. የመጨረሻው የመምረጫ (ድምጽ መስጫ) ሰዓት እና ቀን እሁድ በ 3/12/2023  11፡00 AM ነው።

2ኛ. በ ኦንላይንም (Online) ሆነ በወረቀት ስትመርጡ አንድ ምርጫ የሚቆጠረው እንደ አንድ አባል ስለሆነ ባለቤትዎ ሲመርጡ ከአባል ቁጥር ጎን፟ -2 መጨመር እንዳይረሱ። ምሳሌ M0001-2 

3ኛ. በወረቀት ከመረጡ የአባል ቁጥሮትን እና ስሞትን መምረጫ ወረቀቱ ላይ ይጻፉ።

4ኛ. በኦንላይን (Online) የሚመርጡ ከሆነ ከታች ይተቀመጠውን ሊንክ በመጫን ሎግ አድርገው መምረጥ ይችላሉ።

Member Login – Debre Metemaqe Saint Mary (ethiopianorthodoxchurcharizona.org)

ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር

የሰበካ መንፈሳዊ ምክር ቤት

ውድ የቤተክርስቲያናችን አባላት

የሚቀጥለው እሁድ February 26, 2023 አዲስ የሚቋቋመውን የ ህንጻ ኮሚቴ እጩዎችን ስለምናሳውቅና አዳዲስ ጥቆማዎችም ካሉ ተወያይተን ስለምንወስን በቀኑ ከመደበኛ አገልግሎት በኋላ በምናደርገው ስብሰባ እንዲገኙ በማክበር እናሳስባለን። በዚሁም ስብሰባ እስከዛሬ የተሰራውንም እናስታውቃለን።

ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር

የሰበካ መንፈሳዊ ምክር ቤት