እንደሚታወቀው በአሁኑ ሰዓት በእግዚአብሔር ፈቃድ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራችን እየበዛ የቤተክርስቲያናችን ቦታ እየጠበበን እንገኛለን::ይህንንና ሌሎችንም ችግሮች ለመቅረፍ የቤተክርስቲያናችን የህንፃ ኮሚቴና የሰበካ ጉባኤ አባላት ለረጅም ጊዜ ጥናትና ውይይት ሲያደርጉ ቆይተው ባለን ሰፊ ግቢ ላይ አዲስ ቤተክርስቲያን ለመስራት ወስነዋል::
ይሁንና በቤተክርስቲያናችን መተዳደሪያ ደንብ አንቀፅ 12:3 መሰረት እነዚህ ሁለት ኮሚቴዎች አንድ ላይ ያፀደቁትን ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ሲፀድቅ ስራ ላይ ይውላል ስለሚል አፅዳቂዎቹ እናንተ በመሆናችሁ ዕሁድ October 15th ከቅዳሴ በኃላ በምናደርገው ስብሰባ ላይ ተገኝታችሁ ገለፃውን ሰምታችሁ ድምፅ እንድትሰጡ ስንል በትሕትና እንጠይቃለን!
ማሳሰቢያ፡
የሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ምክር ቤት