
ማሳሰቢያ
በቀን 1/17/2026 እና 1/18/2026 የጥሞቀት በዓልን በመናፈሻ (park) ለማክበር የኦሪዞና ወረዳ ቤተ ክህነት የአደባባይ በዓላት ዝግጅት ኮሚቴ በትጋትና በንቃት በመሥራት ላይ ይገኛል ። ምዕመናኑ ከወዲሁ ማድረግ የሚገባቸውን ግዴታና ጥንቃቄ እንደሚከተለዉ ይሆናል፤
- የመኪና ማቆሚያ በሚፈቅደዉ ሕግና ደንብ (parking rules) መሰረት እንዲያቆሙ። በአካል ጉዳተኞች ማቆሚያና ለታቧታቱ በተያዘ ቦታ (reserved parking) ላይ ማቆም አይፈቀድም። መኪናዎት ማንኛዉም ጉዳት ወይም ስርቆት ቢደርስበት ኮሚቴዉ ተጠያቂ አይሆንም።
- ልጆች እንዳይሮጡና እንዳይወድቁ የመጠበቅ ኃላፊነት የቤተሰብ መሆኑን እንገልፃለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ልጆች ቢወድቁ ወይም ለሚፈጠሩ እክሎች ኮሚቴዉ የማይጠየቅ መሆኑን እናስታዉቃለን።
- ቆሻሻን በቆሻሻ መያዣ ቦታ ይጣሉ።
- የጦር መሣሪያና ስለታም ነገር መያዝ አጥብቆ የተከለከለ ነዉ።
- አልኮል በፓርኩ መጠጣት ወይም መሸጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን።
የአሪዞና ወረዳ ቤተ ክህነት የአደባባይ በዓላት ዝግጅት ኮሚቴ