የተከበራችሁ የደብረምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አባላት በሙሉ
በመጀመሪያ የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን የደብረ ምጥማቅ ቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን ደቂቅ ነቢያት የሕፃናት ክፍል የልደትን በዓል በማስመልከት የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ታሪክ በድራማ ለማቅረብ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀዋል። 
 
ስለዚህ በ 01/08/2023 ከቅዳሴ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የጌታችን መወለድ ታሪክ በጣፋጭ ይህፃናት አንደበት ስለሚቀርብ በሰዓቱ ተገኝታችሁ ህፃናቱን ታበረታቱ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዛችኋል።