በመጀመሪያ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ እና ጥምቀቱ አደረሳችሁ እያልን በፊኒክስ አሪዞና የደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም የኢ/ኦ/ተ ቤተ ክርስቲያን የጥር አስተርእዮ የድንግል ማርያምን በዓለ እረፍት ምክንያት በማድረግ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ጥር 19 – 21 /2015 (January 27 – 29) ታላቅ መንፈሳዊ ጉባዔ አዘጋጅቷል።
በዕለቱ ከተለያዩ አድባራት ጥሪ የተደረገላቸው አበው ካህናት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችና ምዕመናን በሚገኙበት በድምቀት ይከበራል።
መርሃ ግብር
† ዓርብ 1/27/23 ከ4:00 PM ጀምሮ ሥርዓተ ዋዜማ
† ቅዳሜ 1/28/23
ከ4፡00AM ጀምሮ በሥርዓተ ማኅሌት ተጀምሮ የንግሥ በዓል ይካሄዳል።
† እሁድ 1/29/23 ከ 5፡00 AM ጀምሮ ጸሎተ ኪዳን፣ ጸሎተ ቅዳሴ እና ትምህርተ ወንጌል ይካሄዳል። ስለዚህ ይህን አውቀው በዕለቱ በመገኘት የድንግል ማርያም በረከት ተሳታፊ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ስም መንፈሳዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።