2026 በዓለ ጥምቀት በፊኒክስ

ማሳሰቢያ

በቀን 1/17/2026 እና 1/18/2026 የጥሞቀት በዓልን በመናፈሻ (park) ለማክበር የኦሪዞና ወረዳ ቤተ ክህነት የአደባባይ በዓላት ዝግጅት ኮሚቴ በትጋትና በንቃት በመሥራት ላይ ይገኛል ። ምዕመናኑ ከወዲሁ ማድረግ የሚገባቸውን ግዴታና ጥንቃቄ እንደሚከተለዉ ይሆናል፤

  1. የመኪና ማቆሚያ በሚፈቅደዉ ሕግና ደንብ (parking rules) መሰረት እንዲያቆሙ። በአካል ጉዳተኞች ማቆሚያና ለታቧታቱ በተያዘ ቦታ (reserved parking) ላይ ማቆም አይፈቀድም። መኪናዎት ማንኛዉም ጉዳት ወይም ስርቆት ቢደርስበት ኮሚቴዉ ተጠያቂ አይሆንም።
  2. ልጆች እንዳይሮጡና እንዳይወድቁ የመጠበቅ ኃላፊነት የቤተሰብ መሆኑን እንገልፃለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ልጆች ቢወድቁ ወይም ለሚፈጠሩ እክሎች ኮሚቴዉ የማይጠየቅ መሆኑን እናስታዉቃለን።
  3. ቆሻሻን በቆሻሻ መያዣ ቦታ ይጣሉ።
  4. የጦር መሣሪያና ስለታም ነገር መያዝ አጥብቆ የተከለከለ ነዉ።
  5. አልኮል በፓርኩ መጠጣት ወይም መሸጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን።

የአሪዞና ወረዳ ቤተ ክህነት የአደባባይ በዓላት ዝግጅት ኮሚቴ