በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የደብረ መጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አባል የሆኑት ወይዘሮ አክበረት ውድ ባለቤታቸው ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽን፤ ምዕመናን ለቅሶ በመድረስና በመገኘት ከጎናቸው እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የለቅሶ ቦታና ሰዓት፦
- ቦታ፦ በደብረ መጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን አዳራሽ
- ቀናት፦ ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሁድ ድረስ
- ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 (2 PM) እስከ ምሽቱ 1:00 (7 PM) “የሕያዋን ሁሉ አምላክ እግዚአብሔር ለሟቹ ነፍስ ዕረፍተ መንግሥተ ሰማያትን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ደግሞ መጽናናትን ይስጥ።”
በመልአከ ብርሃን ትዕዛዝ የቀረበ