Lesson plan, mezmur list, and youtube link for 01-21-2023

የተከበራችሁ ወላጆች
በቅድሚያ እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን የጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ

የፊታችን ቅዳሜ 1/21/23 የጠዋቱ መደበኛ ፕሮግራም አይኖርም ምክንያቱም ከሰዓት በሁዋላ የከተራ በዓልን ስለምናከብር ቤተሰቦች ሁለት ጊዜ እንዳይመላለሱ ነው በተጨማሪም ለበዓሉ ለሚደረገው ቅድመ ዝግጅት ደጀ ሰላሙ ለምግብ ሥራ ስለምንጠቀምበት ነው በዚህ አጋጣሚ ከቻላችሁ የምግብ ዝግጅቱ ላይም ቢሆን ሌሎች ግልጋሎቶች ላይ እገዛ ለማድረግ ከጠዋት ጀምሮ እንድትተባበሩን በትህትና እንጠይቃለን

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እሁድ ሕፃናቱ እነዚህን ሁለት መዝሙሮች ይዘምራሉ ቅዳሜ ልምምድ ስለማይኖረን እባካችሁ አስጠኗቸው

    1. ነአምን በአብ
    2. ክርስቶስ ተወልደ

እግዚአብሔር የዛው ሰው ይበለን
መልካም በዓል

-ወ/ሮ ሙሉ አይናለም