Nate is Missing

ለደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባላት በሙሉ:: የቤተክርስቲያናችን ልጅ ወጣት ናትናኤል ዮናስ ከጁላይ 4 ጀምሮ ጠፍቶ ቤተሰቦች በጭንቀት ላይ ይገኛሉ:: ሁላችንም ፎቶውን በማሰራጨት እንተባበር። ለነገ ሊቀርብ የነበረው ዓመታዊ ሪፖርት ተሰርዞ በምትኩ እግዚአብሔር በሰላም እንዲያስገኝልን በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የጸሎት መርሐ ግብር  ይኖረናል::

ለ2024 ተመራቂዎች ቤተሰቦች

ለ 2024 ተመራቂዎች ቤተሰቦች በሙሉ የተከበራችሁ ምእመናን በሙሉ። እንደምታውቁት የደብረ ምጥማቅ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በየአመቱ ከኮሌጅ እና ከሀይ ስኩል  የሚመረቁ ወጣቶችን በቤተክርስቲያን ፕሮግራም ተዘጋጅቶ በአባቶች ቡራኬ እንደሚደረግላቸው ይታወቃል። በመሆኑም የዘንድሮው እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ June 23/2024 ለማድረግ ታስቧል። የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ተመራቂዎች እንዳይረሱ በሚል ይህን መልእክት ስናደርስ የተመራቂዎችን ፎቶግራፍ ፣ ሙሉ ስማቸውን እና የተማሩበትን ትምህርት ቤት፣ … [Read more…]